የእለቱ ጥቅስ

«እኛ ግን ነፍሳቸውን ሊያድኑ ከሚያምኑቱ ነን እንጂ ወደ ጥፋት ከሚያፈገፍጉ አይደለንም፡፡» ዕብ.10፡39

Site Last Updated:-Friday 3 September 2010
ቅድመ ገጽ
የጥናትና ምርምር ማእከሉ ሁለተኛ ዓመታዊ ዐውደ ጥናቱን ሊያካሔድ ነው
በተ/ሥላሴ ጸጋ ኪሮስ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ጥናትና መርምር ማእከል ሁለተኛ ዓመታዊ ዓውደ ጥናቱን ከነሔሴ 29 እስከ 30 ቀን 2002 ዓ.ም ያካሒዳል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ...
 
የውጭ ማእከላት ሳምንት በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ዓውደ ርእይ ነገ ይከፈታል
በተ/ሥላሴ ጸጋ ኪሮስ

በማኅበረ ቅዱሳን የውጭ ማእከላት ማደራጃና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀው ዐውደ ርእይ ከነሐሴ 28 እስከ 30 ቀን 2002 ዓ.ም ይካሔዳል፡፡ የውይይት መርሐ ግብርም ተዘጋጅቷል።

በዋናው ማእከል ሕንፃ ላይ የሚካሔደው ዓውደ ርእይ ከኢትዮጵያ ውጭ ያለውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እና የማኅበረ ቅዱሳንን እንቅስቅሴ በዋነኝነት ሲመለከት ያጋጠሙ ችግሮችንም ይዳስሳል፡፡ በተጨማሪም በየአህጉራቱ ያለውን የአኀት አብያተ ክርስቲያናት እንቅስቅሴ፣ የማኅበረ ቅዱሳን የውጭ ማእከላት ማደራጃና ማስተባበሪያ ዋና ክፍል ተግባራት፣ ራእይና ዓላማ ይዳሰስበታል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ...
 
የማኅበረ ቅዱሳን ዘጠነኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተጠናቀቀ
በተ/ሥላሴ ጸጋ ኪሮስና ኪ/ማርያም

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ዘጠነኛ ጠቅላላ ጉባኤ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቀቀ፡፡ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይም ውይይት ተካሂዷል ፡፡  

general_assembly.jpg

 

 

 

 

 

ተጨማሪ ያንብቡ...
 
«የጻድቅ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው።» መዝ 115፥6
Abune_Teklehaimanot.jpg
ይህንን ቃል የተናገረው ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት ነው፡፡ ሞት ለአዳማውያን ሁሉ የማይቀር ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከጠባብ ወደ ሰፊ፣ ከጊዜያዊ ወደ ዘላለማዊ የሚሸጋገሩበት ድልድይ ነው፡፡ ቁም ነገሩ ግን በሃይማኖት በምግባር ጸንቶ ገድል፣ ትሩፋትን ፈጽሞ፣ የክብርን አክሊል ተቀዳጅቶ  በረከትንና ቃል ኪዳንን ተቀብሎ መጠራት የዘላለም ጸጋ የሚያስገኝ ነው፡፡ እንዲህ ዓይነትን ሞት ነው ክቡር ዳዊት «የቅዱሳን ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው» ያለው፡፡ ለዚህ ክብር ከበቁ ቅዱሳን አንዱ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ናቸው።
 

ተጨማሪ ያንብቡ...
 
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክና እምነት አጭር ዳሰሳ
«ኢትዮጵያ» የሚለው ቃል «የተቃጠለ ፊት» የሚል ትርጉም ያለው የግሪክ ጥምር ቃል ነው፡፡ ቃሉን ከግብጽ በስተ ደቡብ እስከ ህንድ ውቅያኖስ ድረስ ያለውን ቦታ ለማመልከት ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀሙበት ሆሜርና ሄሮዱተስ የተባሉት ግሪካውያን የታሪክ ጸሐፊዎች ናቸው፡፡
. . .
«ኦርቶዶክስ» የሚለው ቃል ቀጥተኛ /ትክክለኛ/ የሚል ትርጉም ያለው የግሪክ ጥምር ቃል ነው፡፡ይህንን ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ ለቤተ ክርስቲያን ቅጽልነት /ገላጭነት/ የተጠቀሙት በ325 ዓ.ም በኒቅያ /የዛሬይቱ ኢስታንቡል አጠገብ የምትገኝ ከተማ/ የተሰበሰቡት ጳጳሳትና የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ናቸው፡፡
. . .
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ምንጮች ሦስት ናቸው፡፡ እነዚህም፡-

. . .

ግጻዌ
Difficulty with characters ?
Click here! if you have difficulty reading amharic(geez) characters
ያግኙን
አስተያየት፤ ጥያቄ ወይም ጥቆማ ካለዎት እዚህ ይጫኑ።
ምን ተለወጠ ?