|
የእለቱ ጥቅስ |
|
እስከ ሞት ድረስ የታመንህ ሁን - ራዕ. 2.10 |
|
Site Last Updated:-Friday 3 September 2010 |
|
የማኅበረ ቅዱሳን ጥናት እና ምርምር ማዕከል ሥራውን በይፋ ከጀመረበት ኅዳር ወር 2001 ዓ.ም ጀምሮ የተለያዩ ሥራዎችን የሠራ ሲሆን የሚከተሉት በዋነኛነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
- ወርኃዊ የሥነ ቤተክርስቲያን የውይይት መድረኮችን በማዘጋጀት የሚመለከታቸውን አካላት በማወያየት የመፍትሔ ሐሳብ አመላክቷል፣
| ቀን
|
ርዕስ
|
አቅራቢ
|
አወያይ
|
ቦታ
|
ተሳታፊዎች
|
| ቀን |
ርዕስ |
አቅራቢ |
አወያይ |
ቦታ |
ተሳታፊዎች |
| ኀሙስ፣ ታኅሳስ 30 2001 ዓ.ም. 11፡00 – 1፡00 |
ጥናትና ምርምር ለቤተክርስቲያን አስፈላጊ ነዉን? |
ዲ/ን ዳንኤል ክብረት - የቤተክርስቲያን ተመራማሪ |
ዲ/ን መንግሥቱ ጎበዜ - የታሪክ እና አርኪዮሎጂ ባለሙያ |
የማኅበሩ ቤተ መጻሕፍት |
ከ60 በላይ |
ቅዳሜ፣ ጥር 30 2001 ዓ.ም.
10፡00 – 12፡30 |
የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የራሷ የሆነ የዐሣሣል ዘይቤ አላትን? |
ሠዓሊ አከክሊሉ - የኮተቤ ኮሌጅ መምህር ሠዓሊ በቀለ መኮንን - ሠዓሊ እና አዲስ አበባ ዪኒቨርሲቲ የሥነ ጥበብ መምህር |
ሠዓሊ አበራ መሐሪ - በአዲስ አበባ ት/ት ቢሮ የሥነ ጥበብ ባለሞያ |
የማኅበሩ ቤተ መጻሕፍት |
ከ80 በላይ
|
ቅዳሜ ፣መጋቢት 05 2001 ዓ.ም.
8፡30 – 11፡30 |
የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ቅርሶች እንዴት የጠበቁ? |
ተ/ፕ/ር ሽፈራዉ በቀለ - አዲስ አበባ ዪኒቨርሲቲ በታሪክ እና ቅርስ አስተዳደር ት/ክፍል መምህር |
አቶ ተክሌ ሀጎስ - የቅርስ ቁጥጥር መምሪያ ሓላፊ አቶ ዓለሙ ኃይሌ - የመረጃ እና ምርምር ሓላፊ |
ብሔራዊ ሙዚየም አዳራሽ |
ከ 110 በላይ |
| ዐርብ ፣ሚያዝያ 23 2001 ዓ.ም. |
የቤተክርስቲያን ሊቃዉንት የት ናቸዉ? |
ዲ/ን ዳንኤል ክብረት - የቤተክርስቲያን ተመራማሪ መ/ር በአማን - የቅኔ፣ የዜማ፣ የአቋቋም መምህር |
ዶ/ር ዉዱ - በአዲስ አበባ ዪኑቨርሲቲ የታሪክ ቅርስ አስተዳደር ት/ት ክፍል ሊቀመንበር |
የማኅበሩ አዲሱ ሕንጻ አዳራሽ |
ከ100 በላይ |
| ማክሰኞ፣ሚያዝያ 27 2001 ዓ.ም. 10፡00 – 12፡30 |
የግእዝ ጥናት እና የነገ ተስፋዎቹ |
ዲ/ን መርሻ አለኸኝ - ሀምቡርግ ዩኒቨርሲቲ የፒ.ኤች ዲ. ተማሪ |
መ/ር ደሴ ቀለብ - የጥናትና ምርምር ማዕከል ሓላፊ |
የማኅበሩ ቤተ መጻሕፍት |
ከ65 በላይ |
ቅዳሜ ፣ ሰኔ 06፣ 2001 ዓ.ም.
9፡00 – 11፡30 |
ልመና እና ቤተክርስቲያን |
አቶ መስፍን ይልማ - የምጣኔ ሀብት፣ የከተማ ልማት፣ የሥራ አመራር እና የመልካም አስተዳደር ባለሞያ |
ዶ/ር የራስወርቅ አድማሴ - በአ.አ.ዩ. የሶሾሎጂና ሶሻል አንትሮፖሎጂ ት/ት ክፍል መምህር |
የማኅበሩ አዲሱ ሕንጻ አዳራሽ |
ከ60 በላይ |
- በቤተክርስቲያን ጉዳዮች ላይ በታላላቅ ምሁራን እና ሊቃውንት የተጠኑ ጥናቶች የቀረቡበት የሁለት ቀናት ዓመታዊ ሲምፖዚየም አዘጋጅቷል፡፡
| ቀን
|
ርዕስ
|
አቅራቢ
|
አወያይ
|
ቦታ
|
ተሳታፊዎች
|
| ቀን |
ርዕስ |
አቅራቢ |
አወያይ |
ቦታ |
ተሳታፊዎች |
| ቅዳሜ ፣ ነሐሴ 30 2001 ዓ.ም. 3፡00 – 6፡30 |
የኢትዮጵያ ቅዱሳት ሥዕላት ታሪክ እና አሁን የሚገኙበት ሁኔታ |
አቶ አበባዉ አያሌዉ - በአዲስ አበባ ዪኒቨርሲቲ መምህር |
ዺ/ን ብርሃኑ አድማስ - የሐመር መጽሔት ዋና አዘጋጅ |
ብሔራዊ ሙዚየም አዳራሽ |
ከ 110 በላይ |
| ቅዳሜ ፣ ነሐሴ 30 2001 ዓ.ም. 8፡00 – 9፡30 |
የቤተክርስቲያን የማይንቀሳቀሱ ሀብቶች ሕጋዊ የይዞታ መብት አጠባበቅ |
አቶ ፊሊጶስ ዓይናለም - የሕግ ባለሙያ |
ዲ/ን ዳንኤል ክብረት - የቤተክርስቲያን ተመራማሪ |
ብሔራዊ ሙዚየም አዳራሽ |
ከ 120 በላይ |
| ቅዳሜ ፣ ነሐሴ 30 2001 ዓ.ም. 10፡00 – 11፡30 |
|
ዘላለም ጋረደዉ - የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪ |
ከ 120 በላይ |
| እሑድ ፣ ጳጉሜን 1 2001 ዓ.ም 3፡00 – 4፡30 |
የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን አስተዳደራዊ ችግሮች |
አቶ በድሉ አሰፋ - የሰዉ ኀይል አስተዳደር ባለሙያ |
አቶ ዳዊት - የሥራ አመራር ባለሙያ |
ብሔራዊ ሙዝየም አዳራሽ
|
ከ 120 በላይ |
| እሑድ ፣ ጳጉሜን 1 2001 ዓ.ም 5፡00 – 6፡30 |
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፕትርክና ታሪክ |
ዾ/ር ውዱ ጣፈጠ - በአዲስ አበባ ዪኑቨርሲቲ የታሪክ ቅርስ አስተዳደር ት/ት ክፍል ሊቀመንበር |
|
ከ 120 በላይ |
| እሑድ ፣ ጳጉሜን 1 2001 ዓ.ም. 8፡00 – 11፡30 |
ገዳማት እና አድባራት በደቡብ ኢትዮጵያ |
ተ/ፕ/ር ሽፈራዉ በቀለ - በአዲስ አበባ ዪኒቨርሲቲ በታሪክ እና ቅርስ አስተዳደር ት/ክፍል መምህር |
መ/ር ደሴ ቀለብ - አዲስ አበባ ዪኒቨርሲቲ የቋንቋዎች ጥናት ተቋም መምህር |
ብሔራዊ ሙዚየም አዳራሽ |
ከ 120 በላይ |
- ለማዕከሉ አባላት በሙሉ ስለ ጥናት እና ምርምር ጽንሰ ሐሳብ /Research methodology/ መሠረታዊ ሥልጠና ሰጥቷል፣
- ለአጥኝዎች (ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፣ ለቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች፣ ...) የምክር አገልግሎት ሰጥቷል፣
- ስለ ጥናትና ምርምር አስፈላጊነት ግንዛቤ የመፍጠር እና ማዕከሉን በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን የማስተዋወቅ ሥራ ተሠርቷል፣
- ለማዕከሉ ክፍሎች አዳዲስ አባላትን የማምጣት ሥራ ተሰርቷል፣
- የማዕከሉን እና የቤተመጻሕፍቱን መተዳደሪያ ደንብ አዘጋጅቷል፣
- የቤተክርስቲያን ሊቃዉንትን በመጠኑም ቢሆን በአገልግሎቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ አድርጓል፣
- የተለያየ ሙያ ያላቸዉን ምሁራን ቤተክርስቲያንን ያገለግሉ ዘንድ የሚያገናኝ መድረክ ፈጥሯል፤
- በሥሩ ለሚገኘው አነስተኛ ቤተመጻሕፍት ከግለሰቦች እና ከተቋማት በርካታ መጻሕፍትን አሰባስቧል፡፡
- ከበርካታ የአገር ውስጥ እና የውጭ አገር ተቋማት ጋር ግንኙነት ፈጥሯል፡፡
፪ ማዕከሉ ያከናወናቸው እና የሚያከናዉናቸው ክንውኖች - በ፳፻፪ ዓ.ም.
ይቀጥላል...
|
|
|