የእለቱ ጥቅስ

“... እኔ የጳውሎስ ነኝ፤ እኔ ግን የኬፋ ነኝ፤ እኔስ የክርስቶስ ነኝ ትላላችሁ። ክርስቶስ ተከፍሏልን ?...“ 1ኛ ቆሮ 112-13

Site Last Updated:-Friday 3 September 2010
ከጋምቤላ ክልል የመጡ ሠልጣኞች ተመረቁ

በማኅበረ ቅዱሳን የትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ክፍል አስተባባሪነት ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክና የኑዌር ብሔረሰብ ተወላጅ ሠልጣኞች ተመረቁ፡፡ በማኅበረ ቅዱሳን የትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ዋና ክፍል ሓላፊ ዲ/ን አንዱአምላክ ይበልጣል እንደተናገሩት በክልሉ ከ1997 ዓ.ም ወዲህ ሠልጣኞች መጥተው ሲሠለጥኑ የአሁኑ የመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡

ሓላፊው የሥልጠናውን ዓላማ ሲያስረዱ በአብዛኛው የጠረፋማ ቦታዎች የሚገኙ ብሔር ብሔረሰቦች በቋንቋቸው የሚያስተምራቸው ባለማግኘታቸው ተቸግረው ቆይተዋል፡፡ ይህንን ለማቃለል ከማኅበረሰቡ የተገኙ ወጣቶችን በማስተማር ወደ ትውልድ ቀዬአቸው ተመልሰው ሕዝቡን እንዲያስተምሩና እንዲያስጠምቁ ለማድረግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ላሬ፣ ኝንኛንግ፣ ፒኝዶ፣ አበቦ፣ ጆር፣ ኢታንግ እና ጋምቤላ ዙሪያ ከሚባሉ ሰባት ወረዳዎች የመጡት ሠልጣኞች በቁጥር ዐሥራ ስድስት ሲሆኑ ሥልጠናው ዐሥራ አምስት ቀን እንደወሰደ ሓላፊው ተናግረዋል፡፡

ሥልጠናውን ለመሥጠት ከሰላሳ አምስት ሺሕ ብር በላይ ወጪ እንዳስፈለገ የጠቀሱት ሓላፊው ወደፊትም በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚገኙ በጎ አድራጊዎች ይህንን መሰል መንፈሳዊ አገልግሎት ለማከናወን የእርዳታ እጃቸውን ከዘረጉ በርካታ የጠረፋማ አካባቢ ወገኖችን ለማስተማር እንደሚቻል አስረድተዋል፡፡

በአፍ መፍቻ ቋንቋ ተምሮ ማስተማር ውጤቱ ከፍተኛ በመሆኑም የክርስትናው እምነት ባልተዳረሰባቸው አካባቢዎች በቋንቋቸው በማስተማር ልንደርስላቸው ይገባል ብለዋል፡፡

ሠልጣኞቹ ሥነፍጥረት፣ ትምህርተ ሃይማኖት፣ የቤተክርስቲያን ታሪክ፣ ነገረ ቅዱሳን፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንና የስብከት ዘዴ በሚሉ ርእሶች ትምህርት እንደተሰጣቸው እና ወደ ክልላቸው ሔደው ምን መሥራት እንደሚገባቸው ምክክር እንደተደረገም ለማወቅ ተችሏል፡፡

 
< Prev   Next >
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክና እምነት አጭር ዳሰሳ
«ኢትዮጵያ» የሚለው ቃል «የተቃጠለ ፊት» የሚል ትርጉም ያለው የግሪክ ጥምር ቃል ነው፡፡ ቃሉን ከግብጽ በስተ ደቡብ እስከ ህንድ ውቅያኖስ ድረስ ያለውን ቦታ ለማመልከት ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀሙበት ሆሜርና ሄሮዱተስ የተባሉት ግሪካውያን የታሪክ ጸሐፊዎች ናቸው፡፡
. . .
«ኦርቶዶክስ» የሚለው ቃል ቀጥተኛ /ትክክለኛ/ የሚል ትርጉም ያለው የግሪክ ጥምር ቃል ነው፡፡ይህንን ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ ለቤተ ክርስቲያን ቅጽልነት /ገላጭነት/ የተጠቀሙት በ325 ዓ.ም በኒቅያ /የዛሬይቱ ኢስታንቡል አጠገብ የምትገኝ ከተማ/ የተሰበሰቡት ጳጳሳትና የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ናቸው፡፡
. . .
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ምንጮች ሦስት ናቸው፡፡ እነዚህም፡-

. . .

ግጻዌ
Difficulty with characters ?
Click here! if you have difficulty reading amharic(geez) characters
ያግኙን
አስተያየት፤ ጥያቄ ወይም ጥቆማ ካለዎት እዚህ ይጫኑ።
ምን ተለወጠ ?