የእለቱ ጥቅስ

«አንተ ሰባራውን ጠጋኝ የመኖሪያ መንገድን አዳሽ ትባላለህ፡፡» /ኢሳ.58-12/

Site Last Updated:-Friday 3 September 2010
ማኅበረ ቅዱሳን
መጽሔተ ተልእኮ ዘማኅበረ ቅዱሳን
Metsihete_Teleko.JPG

 
የማኅበረ ቅዱሳን መተዳደሪያ ደንብ
በሐምሌ ወር 1994 ዓ.ም ቅዱስ ሲኖዶስ ያጸደቀው የማኅበረ ቅዱሳን መተዳደሪያ ደንብ

 
ማኅበረ ቅዱሳን በ2001 ዓ.ም
                                               ከማኅበሩ የሕዝብ ግንኙነት አግልግሎት
 
በቅዱስ ሲኖዶስና በብፁዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ መልካም ፈቃድ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሥር ተዋቅሮ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት በማበርከት ላይ የሚገኘው ማኅበረ ቅድሳን በቅዱስ ሲኖዶስ ጸድቆ በተሰጠው መተዳደሪያ ደንብ መሠት ዕውቅና አግኝቶ ከተመሠረተበት ከ1984 ዓ.ም ጀምሮ በማዕከላት በዓመት አንድ ጊዜ ጠቅላላ ጉባኤ ያደርጋሉ፡፡ በዚህም መሠረት በማዕከሉ ሥር ከተዋቀሩት ወረዳ ማዕከላት፣ ግንኙነት ጣቢያዎችና ግቢ ጉባኤያት የተወከሉ ጠቅላላ ጉባኤ ያደርጋሉ፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ...
 
ማኅበረ ቅዱሳን ማን ነው? ክፍል አንድ

ማኅበረ ቅዱሳን ማን ነው? ምንስ እየሠራ ነው? የተዛባ አመለካከት የማይጋርደው ገሐድ እውነታ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሊቃውንት ብራና ዳምጠው፤ ቀለም በጥብጠው፣ ብዕር ቀርጸው በየአብያተ ክርስቲያናቱ የመቃብር ቤቶች ውስጥ በማስተማር ትውልዱ የሀገር መሪ፣ የቤተክርስቲያን አለኝታ፣ የእግዚአብሔር ቅን አገልጋይ እንዲሆን ያበረከቱት አገልግሎት ከዘመን ዘመን እየተሸጋገረ ለትውልድ ሲተላለፍ የኖረና የሚኖር ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለሀገራችን ሥልጣኔ በር ከፋች ሆና የኖረች ከመሆኗም በላይ ዛሬ ላለው ዘመናዊ ሥልጣኔም መሠረት የጣለች ባለውለታ ናት፡፡ ቀደምት የቤተክርስቲያን አበው ደከመን፣ ሰለቸን ሳይሉ ዐረፍተ ዘመን እስከገታቸው ድረስ ሲያገለግሉ ኖረው ቤተክርስቲያኒቱ አሁን ከምትገኝበት የዕድገት ደረጃ አድርሰዋታል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ...
 
ማኅበረ ቅዱሳን ማን ነው? ክፍል ሁለት

የማኅበሩ ዓላማ፣ተግባራትና መዋቅር

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በምትመራበት ቃለ ዓዋዲ መሠረት የተቋቋሙት ሰበካ ጉባኤያት እና ሰንበት ትምህርት ቤቶች የመንፈሳዊ አገልግሎታቸው ተግባራዊ አፈጻጸም በተመሠረቱበት አጥቢያ ብቻ የተወሰነ ነው፡፡ በቃለ ዓዋዲው በተቀመጠው መሠረት የምእመናንም ሆነ የወጣቶች ተግባራት በቤተክርስቲያን መዋቅር ተፈጻሚ መሆናቸው ይታወቃል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ...
 
Difficulty with characters ?
Click here! if you have difficulty reading amharic(geez) characters
ያግኙን
አስተያየት፤ ጥያቄ ወይም ጥቆማ ካለዎት እዚህ ይጫኑ።
ምን ተለወጠ ?