የእለቱ ጥቅስ

«አንተ ሰባራውን ጠጋኝ የመኖሪያ መንገድን አዳሽ ትባላለህ፡፡» /ኢሳ.58-12/

Site Last Updated:-Friday 3 September 2010
ለህጻናት
«ቡሄ! ቡሄ!»

 በመላው ሀገራችን ስለሚከበረው የቡሄ በዓል ጥቂት እናውጋችሁ፡፡

የቡሄ በዓል ትልቅ ታሪክ አለው፡፡ በቤተ ክርስቲያን ዘንድ ደግሞ «ደብረታቦር» እየተባለ ይጠራል፡፡ በየዓመቱ ነሐሴ አሥራ ሦስት ቀን ይከበራል፡፡

ደብረ ታቦር በግዕዝ ቋንቋ ሲሆን የታቦር ተራራ ማለት ነው፡፡ ማቴ 07÷1-8:: የታቦር ተራራ የሚገኘው አሁን ፍልስጥኤም ተብሎ በሚጠራው ሀገር ነው፡፡ ደብረ ታቦር ወይንም የታቦር ተራራ ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስት ደቀመዛሙርቱን ይዞ ወደ ተራራው የወጣበትና ፊቱ እንደፀሐይ የበራበት ልብሱም እንደብርሃን ነጭ የሆነበት ቦታ ነው፡፡
buhea.jpg

 

 

 

 

 

 

 

  ይህ ቦታ ጌታ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት ተራራ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ያቺ ዕለት ቡሄ የሚለውን ስያሜ አገኘች ቡሄ ማለት ገላጣ፣ የተገለጠ ማለት ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...
 
የሙዳዩ ምስጢር

ሁለት ሰዎች ናቸው በአንድ ላይ ሲኖሩ ከዕለታት አንድ ቀን አንድ ሰው መጣና «እናንተ ሰዎች ሆይ» አላቸው «አቤት ጌታችን» አሉት፡፡ ከተቀመጡበት ብድግ ብለው ተቀበሉት፡፡ «አንድ ትልቅ ነገር ላማክራችሁ ነው የመጣሁት» አላቸው፡፡ «ምን» አሉት «ይሔን ሙዳይ አያችሁት?» አላቸው፡፡ «አዎን» አሉት ሙዳዩን ትኩር ብለው እየተመለከቱ እዚህ ሙዳይ ውስጥ ታላቅ ምስጢር አለ፡፡ ሰው ሊያየው የማይችል ነገር ግን እኔ ሩቅ ሀገር ልሔድ ስለሆነ እዚያ ሔጄ እስክመጣ ከፍታችሁ ሳታዩት እናንተ ዘንድ በታማኝነት ልታስቀመጡልኝ ትችላላችሁ?» ሲል ጠየቃቸው፡፡

«እንዴ ለምን አናስቀምጥም እንኳን ከፍተን ልናየው ራሱን ሙዳዩን ካስቀመጥክበት ሣጥን አንተ መጥተህ እስክታነሣው ዞር ብለን ላናየው ቃል እንገባልሀለን» አሉት፡፡ ሰውየው ደስ አለውና ዕቃውን በአደራነት ሰጥቷቸው ሔደ፡፡

እነዚህ ሰዎች ከጥቂት ቀን በኋላ ለምንድን ነው ግን ይሔን ሙዳይ ከፍታችሁ አትዩ ያለን ብለው ተነጋገሩ፡፡ አንደኛው ለጓደኛው «ይሔን ሙዳይ አትዩ ያሉበት ምስጢር ግራ ገብቶኛል አንተስ?» ሲል ጠየቀው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...
 
የሦስቱ ርግቦች ዝማሬ
ከሽዋወርቅ
23/09/2002ዓ.ም.
በድሮ ዘመን ነው የጫካ ገዢ ሆኖ አንድ አውሬ በአንድ ሀገር ያሉ እንስሳትን አራዊትን አዕዋፋትን ሁሉ አንቀጥቀጦ ይገዛቸው ነበር፡፡ ልጆች ታዲያ ይገርማችኋል እሱ አይሠራም አይወጣም፣ አይወርድም ደልቀቅ ብሎ ተኝቶ እንስሳቶቹን ላባቸው ጠፍ እስኪል ምግብ ከያለበት ሰብስበው ያመጡለታል፣ ለራሳቸው ሳይበሉ ሳይጠጡ ቅድሚያ ለእርሱ አቅርበው እሱ በልቶ ጠግቦ ከተረፈው ነው የሚበሉት ጨርሶም ከበላው ሆዳቸው እየተቃጠለ ፀጥ ይሉታል፡፡ 
ተጨማሪ ያንብቡ...
 
ለምን ነጭ እንለብሳለን ?
23/09/2002ዓ.ም.
እሺ ሕፃናት እንዴት ነው አለባበሳችሁ?ሕፃናት... እኛ ኢትዮጵያውያን አለባበሳችን እኮ ልዩ ነው፡፡ አስተውሉ እሺ በተለይ ኦርቶዶክሳውያን ሥርዓተ ሃይማኖታችን የመላእክት ሥርዓት ነው፡፡ «እንዴት ?» በሉኝ፡፡ ጐሽ ሕፃናት! ... በጣም ጥሩ ጥያቄ ነው፡፡

ለምሳሌ ብጠቅስላችሁ ዜማችን የመላእክት ዜማ ነው፡፡ የቅዱስ ዮሐንስን ራእይ መጽሐፍ ብታነቡ ቅዱሳን መላእክት ማዕጠንት ይዘው በመሰንቆ በበገና አመሠገኑት ይላል፡፡ ሌላም ብዙ ብዙ ሥርዓቶች የመላእክት ናቸው፡፡ የቤተ ክርስቲያናችንም ሥርዓት ይህንኑ መሠረት ያደረገ ነው፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ...
 
ሕፃናት በቤተ ክርስቲያን

 22/09/2002 ዓ.ም.

ልጆች ሕፃናት በቤተ ክርስቲያን በሚል ርዕስ አጭር ትምህርት እናቀርብላችኋለን። በደንብ ተከታተሉ፡፡ እሺ? ጐበዞች፡፡

በመጀመሪያ ሕፃናት ማለት ምን ማለት ነው? ንጹሕ ልቡና ያላቸው ክፉንና ደጉን ያልለዩ፣ ራሳቸውን ያልቻሉ በቤተሰብ እቅፍ ውስጥ ያሉ እንክብካቤ የሚያስፈልጋቸው ሕፃናት ይባላሉ፡፡
ቤተ ክርስቲያን ማለት ደግሞ፡- የክርስቲያኖች መሰብሰቢያ፣ አምላካችን እግዚአብሔርንና እመቤታችንን የሚወደሱበት ሐዋርያት፣ ጻድቃን፣ ቅዱሳን የሚመሰገኑበት፣ የእግዚአብሔር ቃል ዕለት ዕለት የሚነገርበት፣ ሰዎች ከክፉ ነገር ሁሉ ተቆጥበው ራሳቸውን ከኃጢአት የሚቆጥቡበት የተቀደሰ ቦታ ማለት ነው፡፡

ሕጻናት ወደ ቤተ ከርስቲያን ለምን ይመጣሉ? ጸጋ እግዚአብሔርን እንዲያገኙ፣ መንፈሳዊና ዘመናዊ ጥበብ ዕውቀት እንዲገለጽላቸው፣ እግዚአብሔር እንዲባርካቸው፣ ለራሳቸው ለቤተሰባቸው ለሀገርና ለሕዝባቸው ታማኝና ጨዋ ሆነው እንዲገኙ፣ በመንፈሳዊ ሕይወት /ትምህርት/ ተኮትኩተው ጥሩ ዜጋ እንዲሆኑ ለታላላቆቻቸው፣ ለእናትና አባታቸው ታዛዥ ለእኩዬቻቸው ምሳሌ /አርአያ/ እንዲሆኑ፣ መጥፎ ነገር ፈጽሞ እንዳያስቡ ነው፡፡ ጥሩ ጥሩ ጨዋታ እየተጫወቱ የሚያድጉ የዛሬ አበባዎች የነገ ፍሬዎች ሕፃናት ናቸውና ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ትወዳቸዋለች፣ ትንከባከባቸዋለች፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...
 
<< መጀመሪያ < ወደኋላ 1 2 ወደፊት > መጨረሻ >>

ውጤቶች 1 - 9 ከ 11
Difficulty with characters ?
Click here! if you have difficulty reading amharic(geez) characters
ያግኙን
አስተያየት፤ ጥያቄ ወይም ጥቆማ ካለዎት እዚህ ይጫኑ።
ምን ተለወጠ ?