|
፩ ማዕከሉ ያከናወናቸው ክንውኖች - በ፳፻፩ ዓ.ም.
የማኅበረ ቅዱሳን ጥናት እና ምርምር ማዕከል ሥራውን በይፋ ከጀመረበት ከኅዳር ወር 2001 ዓ.ም ጀምሮ የተለያዩ ሥራዎችን የሠራ ሲሆን የሚከተሉት በዋነኛነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
- ወርኃዊ የሥነ ቤተክርስቲያን የውይይት መድረኮችን የሚመለከታቸውን መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን በመጋበዝ አካሂዷል
|
|
ተጨማሪ ያንብቡ...
|
|
|
፩ የጥናትና ምርምር ማዕከሉ መመሥረት
ጥናትና ምርምር በሳይንሳዊ ዘዴ ለችግር መፍትሔ ለማፈላለግ፣ አዳዲስ ግኝቶችን ለመፍጠር፣ ተጨማሪ ዕውቀትን
ለማግኘት፣ አስፈላጊውን መረጃ ይዞ ተገቢውን ውሳኔ ለመስጠት የሚያስችል ዐቢይ ተግባር ነው፡፡ ዛሬ አንቱ የተባሉ፣
ዓለምን ያስደመሙ ጥበባት ኹሉ የጥናትና ምርምር ውጤቶች ናቸው፡፡ በዘመናችን በዓለም ላይ የተጋረጡ በርካታ
ማኅበራዊ፣ ምጣኔ ሀብታዊ፣ አካባቢያዊ፣ ፖለቲካዊና መሰል ችግሮችን ለመፍታት ዋነኛው መንገድ ጥናትና ምርምር መሆኑ
ግልጽ ነው፡፡ በሀገራችንም ይህንን የሚያስፈጽሙ አያሌ ተቋማት ተመሥርተዋል፡፡ የሥልጣኔ ምንጭ የበርካታ ቅርሶች
ባለቤት ለሆነችው ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የጥናትና ምርምር ሥራ ታላቅ ፋይዳ ያለው መኾኑ
አያጠራጥርም፡፡ ዛሬ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ የታሪክ ባላንጣዎች፣ የቅርስ ዘራፊዎች፣ የበዙበት ነው፡፡ በዚህ ዘመን
እውነቱን ከሐሰት፣ ስንዴውን ከእንክርዳድ፣ በጉን ከተኩላ፣ ማሩን ከእሬት በመለየት ትክክለኛውን የኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ሳይዛነፍ፣ ሳይቀየጥ፣ በክብር ጠብቆ ለተተኪው ትውልድ ለማስተላለፍ
ይቻል ዘንድ የጥናትና ምርምር ሥራ እጅግ በጣም ወሳኝ ነው፡፡
|
|
ተጨማሪ ያንብቡ...
|
|
|