የእለቱ ጥቅስ

መጠራታችሁን ተመልከቱ 1ቆሮ.1፡26

Site Last Updated:-Friday 3 September 2010
ርዕሰ አንቀጽ
ተክሎቻችንን ለፍሬ እናብቃቸው
 
የተወደዳችሁ ምእመናን........
 
ልጆቻችሁ ከመዝሙር ጋር ሃይማኖታቸውን፣ ሥነምግባራቸውን እንዲማሩ ያስፈልጋል፡፡ ወደ ቤተ ክርስቲያን ስትመጡ ልጆቻችሁን ይዛችሁ ኑ፡፡ ብቻችሁን ከመጣችሁ የምትሠሩትን አያውቁም፤ ወዴት እንደሔዳችሁ አያውቁም፡፡ ወራሾቻችሁ አይሆኑም፡፡ አሳዩአቸው፡፡ ሥዕሉን ይሳሙ፤ ቅዳሴ ጠበል ይጠጡ፡፡ በእምነቱ አሻሹአቸው፤ መስቀል እንዲስሙ አስተምሯቸው፡፡ የሚታጠነውን ዕጣኑን ያሸትቱ፤ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ይቀበሉ፤ ቃጭሉ፣ ደወሉ ሲደወል ይስሙ፤ ቄሳቸው ማን እንደሆነ፣ ቤተ ክርስቲያን ምን እንደሆነች፣ በውስጧ ምን ምን እንደሚሠራ ያጥኑ፤ ይማሩ፡፡ ወደ ሰንበቴም ስትሔዱ ይዛችኋቸው ግቡ፤ እነርሱም ነገ ይህን እንዲወርሱ፤ የነገ ባለአደራዎች መሆናቸውን እንዲያውቁ ይማሩ፡፡
 
ማኅበሩ፣ ዝክሩ፣ ሰንበቴው፣ በቅዱሳን ስም በበዓል መሰብሰቡ፣ ማስቀደሱ፣ መቁረቡ፣ ቅዳሴ ጠበል መጠጣቱ፣ መስቀል መሳለሙ..... አባቶቻችንና እናቶቻችን ሥርዓታችንን እምነታችንን ሁሉ ሰፍረው ቆጥረው አስረክበውናል፡፡ እና ይህ ትውልድ ይህንን እንዳያጣ ነው አደራ የምንለው፡፡ ይህ ትውልድ ይህንን ከቀበረ በኋላ፣ ይህንን ካጠፋ በኋላ... ሃይማኖቱን ፍለጋ፣ ታሪኩን ፍለጋ ወደ ቤተ መዘክር እንዳይሔድ ነው፡፡
 
ስለዚህ እምነታችሁን፣ ሥርዓታችሁንና መንፈሳዊ ውርሳችሁን እንድትጠብቁ አደራዬ የጠበቀ ነው፡፡

ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ የሸዋ ሃገረ ስብከት ሊቀጳጳስ /1932 ዓ.ም - 1982 ዓ.ም./ በሻሸመኔ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሚያዝያ 23 ቀን 1982 ዓ.ም ተገኝተው ለምእመናን ከሰጡት ትምህርት የተወሰደ ነው፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ...
 
በስደት የትውልድ ሓላፊነት
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሐዋርያት የፈጸሙትን ተግባር ቀዳሚ ሥራዋ አድርጋ የዘመናትን ድንበር እየተሻገረች አገልግሎቷን ስታከናውን ቆይታለች፡፡ የወንጌልን ብርሃን ላልደረሳቸው ሁሉ ታደርሳለች፡፡ ተምረው ያመኑትን፤ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቀች፤ የመንፈስ ቅዱስን ልጅነት እንዲያገኙ፣ በክርስቶስ ክርስቲያን እንዲሆኑ ታደርጋለች፡፡ በሀገር ውስጥም ይሁን ከሀገር ውጪ በመላው ዓለም በዝርወት /በስደት/ ያሉ ልጆቿን እስከመጨረሻው ትጠብቃለች፡፡ የዘላለማዊው ሕይወት የሰማያዊው መንግሥት ወራሾች እንዲሆኑም ታበቃለች፡፡

የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በውጪው ዓለም የምታከና ውነው ዘርፈ ብዙ መንፈሳዊ አገልግሎትም የሐዋርያዊ ተልእኮዋ አካል ነው፡፡ በተለይም በሰሜን አሜሪካ የቅድስት ቤተክርስቲያን ሐዋርያዊ ጉዞ ዘመናትን አስቆጥሮ አሁን ያለበት ደረጃ ላይ ቢደርስም፤ በአስቸጋሪ ፈተናዎችና ውጣ ውረዶች ውስጥ ማለፍን እና ጽናትን ጠይቋል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ...
 
የቁጭታችን መወጫ
የኢትዮጵያ ቤተመጻሕፍትና ቤተመዛግብት ኤጀንሲ በግእዝ ቋንቋ የተጻፉ ጥንታውያን መጻሕፍትን በመተርጎም ለጥናትና ምርምር ማቅረብ መጀመሩን መነሻ በማድረግ፤ ቀዳሚ የትርጉም ሥራውን «መጽሐፈ ምስጢር»ን ለኅትመት አብቅቶ ሰሞኑን ማስመረቁ ይታወቃል፡፡

በኢትዮጵያ የሥነ ጽሑፍ ታሪክ «ወርቃማው ዘመን» ተብሎ የሚጠራው ዘመን ታላቅ ደራሲ፣ ሊቅ፣ መምህር፣ የምሕንድስና ባለሙያ እና ጻድቅ ከሆነው የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /1357-1426 ዓ.ም/ በርካታ ተጠቃሽ የድርሰት ሥራዎች መካከል «መጽሐፈ ምስጢር» አንዱ ነው፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ...
 
የተግባራዊ መፍትሔ ቀዳሚ ምዕራፍ
በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ አገልግሎትና ልማት ዋና ክፍል አዘጋጅነት የአብነት መምህራን የምክክር ጉባኤ ለሁለተኛ ጊዜ ከሚያዝያ 27 እስከ ግንቦት 1 ቀን 2002 ዓ.ም. ድረስ በአዲስ አበባ መንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አዳራሽ ተካሒዷል፡፡ በዚህ ጉባኤ ላይ በመላው ሀገሪቱ፤ በሰሜን፣ በደቡብ፣ በምሥራቅ፣ በምዕራብ ከሚገኙ ሰባ አምስት ያህል የአብነት ትምህርት ቤቶችና ከታላላቅ የማስመስከሪያ ጉባኤ ቤቶች የመጡ ከሰማንያ በላይ ሊቃውንት /መምህራን/ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ በምክክር ጉባኤው መዝጊያ መርሐ ግብር ላይም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ እንዲሁም ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጭምር ተገኝተዋል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ...
 
ታሪካዊው ትምህርት ቤት ፈጣን ምላሻችንን ይጠብቃል
ከሠላሳ ስምንት በላይ ሊቃነ ጳጳሳት፣ በርካታ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንን እንዲሁም ምሁራንን ያፈራው፤ በአዲስ አበባ ሀገረስብከት ታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም የሚተዳደረው መምህራንና ካህናት ማሠልጠኛ ሕልውናው ፈተና ላይ ወድቆ በከፍተኛ ችግር ውስጥ ይገኛል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ...
 
<< መጀመሪያ < ወደኋላ 1 2 3 ወደፊት > መጨረሻ >>

ውጤቶች 1 - 9 ከ 21
Difficulty with characters ?
Click here! if you have difficulty reading amharic(geez) characters
ያግኙን
አስተያየት፤ ጥያቄ ወይም ጥቆማ ካለዎት እዚህ ይጫኑ።
ምን ተለወጠ ?