|
እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ልደት እና ለማኅበረ ቅዱሳን የምሥረታ በዓል በሰላም አደረሰን፡፡ |
|
በ2002 ዓ.ም ማኅበረ ቅዱሳን ምን ሠራ?
|
|
|
የጽ/ቤት ግንባታ ለማኅበሩ አገልግሎት መፋጠን |
|
ማኅበራችን ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ በርካታ ሥራዎችን እንዲከናወንና እያከናወነ እንዳለ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ አገልግሎቱን በስፋትና በተቀላጠፈ ሁኔታ ለማስኬድ የጽ/ቤት ግንባታው ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ መሆኑ እሙን ነው፡፡
እንደ ልዑል እግዚአብሔር ፈቃድ ዛሬ እዚህ ላይ ደርሰናል፡፡
|
|
|
የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጐ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሁን |
|
2ኛጢሞ.3÷16
እግዚአብሔር ሰውን የፈጠረበት ከውድቀትም ያዳነበት ዋነኛ ዓላማው የፈጠረው ሰው የክብሩ ተካፋይ፣ የመንግሥቱ ወራሸ
እንዲሆን ነው፡፡ ለዚህ ታላቅ ጸጋ የምንታጭባት፣ የምንዘጋጅባትና የምንበቃባት የተቀደሰች ዐውድ ደግሞ ቅድስት ቤተ
ክርስቲያን ነች፡፡
ቤተ ክርስቲያን የሚመሯት እረኞች ካህናትና የመንጋው /ምእመናን/ ኅብረት ናት፡፡ በዚህች አንድ አካል በሆነች ቤተ
ክርስቲያን ምእመናን የተለያዩ ብልቶች ሆነው፣ ህልውናዋ ተጠብቆ ሺሕ ዘመናትን ተሻግራለች፡፡ እነዚህ የተለያዩ
ብልቶች የተባሉ በክርስቶስ አምነው የተሰበሰቡ ልጆቿ የተለያየ የአገልግሎት ጸጋ ያላቸው፣ በዓለሙም ለሥጋቸው
ሠርተው የሚበሉበት የተለያየ ሙያ ያላቸው ብዙ ዜጐቿ ናቸው፡፡
|
|
ተጨማሪ ያንብቡ...
|
|
|
መልካሙን አደራ በእኛ በሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ ጠብቅ |
|
/2ጢሞ.1÷14/
በዘመነ ሐዋርያት ክርስትናን የተቀበለችው ሀገራችን ኢትዮጵያ ለረጅም ዘመናት በግብጽ ቤተ ክርስቲያን ስትመራ
ብትቆይም ሃይማኖቱንና የሃይማኖቱን ሥርዓት በመጠበቅና በማስጠበቅ በኩል ግን ሙሉ በሙሉ ድርሻውን የኢትዮጵያ
ክርስቲያኖችና ነገሥታቱ እንደወሰዱ ይታወቃል፡፡ ከሁለት ሺሕ ያህል ዘመናት ጥረት በኋላ ከሃምሳ ዓመታት በፊት
በራሷ ቅዱስ ሲኖዶስና ፓትርያርክ የመመራት ዕድሉን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ያገኘችው ቤተ ክርስቲያናችን ከራሷ
ወገን በሆኑ ጳጳሳት የራሷን ሃይማኖታዊና አስተዳደራዊ ጉዳዮች እየወሰነች ለመሔድ በቅታለች፡፡
|
|
ተጨማሪ ያንብቡ...
|
|
|
ምርጫችን አንድ ነው፤ ቀጭኑ መንገድና ጠባቡ በር ብቻ |
|
/ማቴ.7÷13/
ከልደተ ክርስቶስ በኋላ ሁለት ሺሕ ዓመታትን አሳልፈን ሦስተኛውን ሺሕ ከጀመርን አንድ ዓመት አስቆጥረናል፡፡ ሁለተኛውን ዓመት ደግሞ በእግዚአብሔር ቸርነት ለመጀመር በቅተናል፡፡ ከመጀመሪያው ተነሥተን አምስት መቶውን ዓመት ያሳለፍነው በዐፄ ካሌብ /በዘመኑ ጳጳስ አልነበረም/ ዘመን ነበር፡፡ ያ ዘመን ክርስትናችን ለፍሬ የበቃበት፣ ለናግራንና ለየመን ክርስቲያኖች እፎይታን ያስገኘንበት፣ ከውስጥ ቅዱስ ያሬድ የተነሣበት፣ ከውጭ ዘጠኙ ቅዱሳንና ሌሎች ቅዱሳንም ሰላም ለማግኘት ወደ እኛ የመጡበት ታሪካዊና የመንፈሳዊ ሕይወትም ከቅድስና ወደ ቅድስና የተሸጋገረበት ወቅት ነበር፡፡ ስለዚህ ነገሥታትና ልጆቻቸው ሳይቀር ከቤተ መንግሥት እየወጡ ወደ ገዳማት /በረሃ/ የገቡበት ዘመነ ተጋድሎ ነበር፡፡ ከመጀመሪያው አምስት መቶ ወደ ሁለተኛው አምስት መቶ በዚሁ የጽድቅ ጎዳና ተሸጋገርን፡፡ /ጉዞ በጠባቡ በር/፡፡
|
|
ተጨማሪ ያንብቡ...
|
|
|
|
<< መጀመሪያ < ወደኋላ 1 2 ወደፊት > መጨረሻ >>
|
| ውጤቶች 1 - 9 ከ 10 |