"እግዚአብሔር በአንድም መንገድ በሌላም ይናገራል።" ኢዮ.33፥14

ባሕረ ሐሳብ የዘመን መቁጠሪያ

ይህ ሶፍትዌር ከዚህ በፊት 2000 .. /..አ. በ2008 / በተለቀቀው ሶፍትዌር ላይ አንዳንድ ማስተካከያዎች በማድረግ ማተም /ፕሪንት ማድረግ/ ንዲቻል ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው። ወደ ኮምፒዩተርዎ በመጫን ይጠቅሙ።

BahireHasabSetupIcon.JPG ሶፍትዌሩን እዚህ በመጫን ይጠቅሙ።

የትንሣኤ ሰላምታ

yetnsaeselamta2in1


 
ቅዱስ ፓትርያርኩ የትንሣኤን በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ

ሚያዚያ 11 ቀን 2006 ዓ.ም.


a2006 1"ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሰዶም ግብረ ኃጢአትን በጽናት መመከት አለበት" ብፁፅ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ


ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የ2006 ዓ.ም. የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓልን የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ፡፡


ቅዱስነታቸው በልዩ ጽ/ቤታቸው በሰጡት መግለጫ “በአዳም አለመታዘዝ ምክንያት ያጣናት ሕይወት፤ በክርስቶስ መታዘዝ አገኘናት፡፡ . . . የእርሱ ትንሣኤ የትንሣኤያችን ዋዜማ ነውና የቀደመችው ሕይወት እንደተመለሰችልን አየናት፤ አወቅናትም” /ኤፌ.4፤ 5-7/ በማለት ገልጸዋል፡፡


ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን በማናቸውም ጊዜ ከነውረ ኃጢአትና ከርኩሰት ሁሉ ርቀው፤ ሕገ ተፈጥሮንና ሕገ እግዚአብሔርን ጠብቀው መኖራቸውን የጠቀሱት ቅዱስነታቸው የሰዶም ግብረ ኃጢአትን ሁሉም ኢትዮጵያዊ በጽናት መመከት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡


መግለጫውን ከዚህ በታች አቅርበነዋል፡-

ዝርዝር ንባብ...
 
የትንሣኤው ትርጉም በዓሉና አከባበሩ

ከሊቀ ትጉሃን ኀ/ጊዮርጊስ ዳኘ
በጠ/ቤተ ክህነት የዕቅድና ልማት መምሪያ ምክ/ሓላፊ

  • «ትንሣኤ» የሚለው ቃል የግእዝ ቋንቋ ነው፡፡

  •  መገኛ ቃሉም «ተንሥአ» = ተነሣ የሚለው ግሥ ይሆናል፡፡

  • «ትንሣኤ» ማለት ታዲያ = መነሣት፣ አነሣሥ ሐዲስ ሕይወት ማግኘት ማለትን ያመለክታል፡፡

  •  «ትንሣኤ» በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በየመልኩ፣ በየዐይነቱ ሲተረጐም ዐምስት ክፍል አለው፡፡

  • «ትንሣኤ» የሚለው ቃል የግእዝ ቋንቋ ነው፡፡

  • መገኛ ቃሉም «ተንሥአ» = ተነሣ የሚለው ግሥ ይሆናል፡፡

  • «ትንሣኤ» ማለት ታዲያ = መነሣት፣ አነሣሥ ሐዲስ ሕይወት ማግኘት ማለትን ያመለክታል፡፡

  • «ትንሣኤ» በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በየመልኩ፣ በየዐይነቱ ሲተረጐም ዐምስት ክፍል አለው፡፡

ዝርዝር ንባብ...
 
ቀዳም ሥዑር

ሚያዝያ 6፣2004 ዓ.ም.

ቅዳሜ፡-

ቀዳም ሥዑር ይባላል፡፡ በዚች ዕለች ከድሮው በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረችው ቅዳሜ ትባላለች፡፡


የማትጾመዋ ቅዳሜ ስለምትጾም ስዑር /የተሻረች/ ተብላለች በዓል መሻርን አይመለከትም በቀዳም ሥዑር  ሌሊት ሥርዓቱ የሚጀመረው በመኀልየ ሰሎሞን ምንባብ ነው፡፡ ማኀሌቱም እዝሉ እየተቃኘ እየተመጠነ፣ እየተዘመመ እየተመረገደ እየተጸፋ ያድራል፡፡ ጥዋት አቡን መዋሥዕት ውዳሴ ማርያም ዜማ ተደርሶ ወለመልአከ ሕይወትሰ ሰቀልዎ በሚለው ሰላም ይጠናቀቃል፡፡በዚህ ዕለት ልብሰ ተክህኖ የለበሱ ካህናትና ዲያቆናት ቄጤማ ተሸክመው ቃጭል ሲያቃጨሉ መታየታቸው ዕለተ ትንሣኤውን ለሚናፍቅ ምእመን ትልቅ ብስራት ነው፡፡

 

ዝርዝር ንባብ...
 
ከጲላጦስ አደባባይ እስከ ሊቶስጥራ

 
ዝርዝር ፅሁፍ...
<< ጀምር < ወደኋላ 1 2 ወደፊት > መጨረሻ >>

ገጽ 1 ከ 2

Difficulty with characters ?

Click here! if you have difficulty reading amharic(geez) characters

ጾም- ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ

የጽሑፎች ማውጫ - በወራት